Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሌማት ትሩፋትን ይበልጥ ለማስፋፋት በትኩረት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግስት የሌማት ትሩፋትን ይበልጥ ለማስፋፋት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በኡራ ወረዳ አምባ አንድ ቀበሌ የማህበረሰብ አቀፍ የሌማት ትሩፋት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታን ተመልክተዋል፡፡

አቶ አሻድሊ በዚህ ወቅት የአልሃልዋ የማህበረሰብ ልማት አቀፍ የተቀናጀ የሌማት ትሩፋት መንደር የዶሮ እርባታ፣ የከብት እርባታ፣ የፍየል እርባታ፣ የንብ እርባታና የመኖ ማቀነባበሪያ ማዕከል ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መንግስት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ እያደረገ የሚገኘውን የሌማት ትሩፋት የበለጠ ለማስፋፋት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ለአካባቢው ማህበረሰብ በስፋት ወተት፣ እንቁላል፣ ማር፣ የደለቡ ፍየሎችና በጎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የማስፋፊያ ግንባታ እየተሰራ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት፡፡

በተጨማሪም ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ፣ የኡራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታጃዲን መሀመድ በሆሃ አነስተኛ መስኖ ልማት ግንባታ እየለማ ያለውን የቀይ ሽንኩርት ልማት ጎብኝተዋል፡፡

Exit mobile version