አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የነበሩት የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሃሙድ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሃሙድ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፥ በይፋዊ ጉብኝታቸው ወቅት የሁለትዮሽ ግንኙነቶቻችንን ለማጠናከር ውጤታማ ውይይቶች ካደረግን በኋላ ዛሬ ከሰዓት ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሃሙድን ሸኝቻለው ብለዋል።