አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በስፔን ሱፐር ካፕ ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና (ኤልክላሲኮ) የሚያደርጉት የፍጻሜ ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ጨዋታው በሳዑዲ ኪንግ አብዱላህ ስፖርት ሲቲ ስታዲየም ምሽት 4 ሰዓት ይደረጋል፡፡
በሱፐር ካፑ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ባርሴሎና አትሌትክ ቢልባኦን እንዲሁም ሪያል ማድሪድ ሪያል ሞዮርካን በማሸነፍ ለዛሬው የፍጻሜ ጨዋታ ደርሰዋል፡፡
በኤልክላሲኮ የመጀመሪያ ዙር የላሊጋ ጨዋታ ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን 4 ለ 0 ማሸነፉ አይዘነጋም፡፡