Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከ60 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ የውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ ከ60 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ።

በምርቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን እንደገለጹት፤ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማሻሻልና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው።

የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በዘላቂነት አግልግሎት እንዲሰጥ ህብረተሰቡ በውሃ ምንጩ አካባቢ የተፈጥሮ ልማት ሥራዎችን መስራት፣ የተዘረጉ የውሃ መስመሮች ከብልሽት መጠበቅና መንከባከብ ይኖርበታል ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በቀጣይ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

የፕሮጀክቱ ለአገልግሎት መብቃት የህብረተሰቡን የዓመታት የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግርን የፈታ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አሊ መኮንን መሆናቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

Exit mobile version