አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና እና ፋሲል ከነማ አንድ አቻ ተለያዩ፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ብሩክ በየነ ለሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ማርቲን ኪዛ ለፋሲል ከነማ ግቦቹን አስቆትረዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕና የሊጉን መሪነት ለመቻል ሲያስረክብ በአንፃሩ የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ቡድን ፋሲል ከነማ ነጥብ በመጋራት ሶስት ደረጃዎችን ማሻሻል ችሏል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተከናወነ ሌላ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 አሸንፏል።
መሀመድ አበራ እና ሚሊዮን ሰለሞን የኢትዮጵያ መድህንን ግቦች ሲያስቆጥሩ፤ ብዙአየሁ ደምሴ ብቸኛዋን የወላይታ ድቻ ግብ አስቆጥሯል፡፡