የሀገር ውስጥ ዜና

የፋና ላምሮት አሸናፊው እዮቤል ፀጋዬ በትውልድ ከተማው ጎንደር አቀባበል ተደረገለት

By Mikias Ayele

January 11, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋና ላምሮቱ ምዕራፍ 18 አሸናፊው እዮቤል ፀጋዬ በትውልድ ከተማው ጎንደር ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።

ለድምፃዊው የጎንደር ባህል ማዕከል የሥራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የማዕከሉ የሙያ አጋሮች እንዲሁም አድናቂዎቹ ናቸው አቀባበል ያደረጉለት።

እዮቤል ፀጋየ ላለፉት ሶስት ወራት በአስደናቂ ተወዳዳሪዎች መካከል ሲካሄድ የቆየው የፋና ላምሮት ምዕራፍ 18 ውድድር ታሕሣሥ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ፍጻሜውን ሲያገኝ ያሸነፈው እዮቤል ፀጋዬ የ400 ሺህ ብር ሽልማት እንደተበረከተለት ይታወሳል፡፡

በምናለ አየነው