Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የካድፕ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በመሪዎች ደረጃ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም (ካድፕ) አስቸኳይ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በስብሰባው ላይ የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ፤ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት ጨምሮ የህብረቱ አመራሮች፣ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የግብርና ሚኒስትሮች፣ የልማት አጋሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፥ በአፍሪካ ህብረት እና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ እና የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ኢትዮጵያን ወክለው በስብሰባው ላይ እየሳተፉ ይገኛል።

በስብሰባው የካድፕ ያለፉት 10 ዓመታት አፈጻጸም የሚገመገም ሲሆን፤ በፈረንጆቹ ከ2026 እስከ 2035 የሚተገበረው የካዳፕ ስትራቴጂ እና የድርጊት መርሃ ግብር እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።

ዘላቂ የምግብ ምርታማነት፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ የግብርናና ኢንዱስትሪ ልማት፣ ሁሉን አቀፍ የዜጎች ተጠቃሚነት፣ የማይበገር የምግብ ስርዓትን ግንባታ እና የመንግስትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ውይይት ከሚደረግባቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ።

የመሪዎቹ ስብስባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version