የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች የፖሊስ አባላት ሕዝብን በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው አስገነዘቡ

By Meseret Awoke

January 11, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ለ29ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን መደበኛ የፖሊስ አባላት ዛሬ አስመርቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምረቃው ላይ÷ ተመራቂ የፖሊስ አባላት የመዲናዋን ሕዝብ በሙያዊ ሥነ-ምግባርና በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

መዲናዋን የሚመጥን ጠንካራ የፖሊስ ኃይል በመገንባት ረገድም በብቁ የሰው ኃይል፣ በሎጂስቲክስና በቴክኖሎጂ የተደራጀ ተቋም እየተፈጠረ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ዛሬ የተመረቁ የፖሊስ አባላትም የተጣለባቸውን ሕዝባዊና መንግሥታዊ አደራ በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በበኩላቸው፥ የአዲስ አበባ ፈጣን ዕድገትን ታሳቢ ያደረገ የወንጀል መከላከል ሥራ በተጠናከረ መልኩ እየተተገበረ መሆኑን ገልጸዋል።