የሀገር ውስጥ ዜና

በሳይበር ደኅንነትና ተያያዥ ዘርፎች የሰለጠኑ ባለ ልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎች ተመረቁ

By Meseret Awoke

January 11, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ለ3ኛ ጊዜ በሳይበር ደኅንነትና ተያያዥ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 237 ባለልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

ተመራቂዎቹ ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ መሆናቸው እና በሥልጠናው በነበራቸው ቆይታ በሳይበር እና ተያያዥ መስኮች በቂ ዕውቀት ማግኘታቸው ተገልጿል፡፡

በዕለቱም የ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደሮች የማሕበረሰብ ተሳትፎ የቅዳሜና ዕሁድ የስልጠና መርሐ-ግብር ተጀምሯል።

በወንድሙ አዱኛ