የሀገር ውስጥ ዜና

ብሪታኒያ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር በመስራት ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማፋጠን ያላትን ቁርጠኝነት ገለጸች

By Feven Bishaw

January 10, 2025

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብሪታኒያ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር በመስራት ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማፋጠን ያላትን ቁርጠኝነት ገለጸች።

በብሪታኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብሩክ መኮንን ከብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ሎርድ ኮሊንስ ጋር ለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወያይተዋል።

ዛሬ ስራ የጀመረውን የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ አስመልክቶ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት በኤክስ ገጻቸው ያሰፈሩት ሎርድ ኮሊንስ፤ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር በመስራት ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማፋጠን ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ተመርቆ መከፈቱ ይታወቃል።