Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

መቻል ስሑል ሽረን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስሑል ሽረ በመቻል 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡

የመቻልን ግቦች ሽመልስ በቀለ በ24ኛው እንዲሁም ግሩም ሀጎስ በ39ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

የስሑል ሽረን የማስተዛዘኛ ግብ ደግሞ አስቻለው ታመነ በ53ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ አስቆጥሯል፡፡

የዛሬው የመጨረሻ የጨዋታ መርሐ-ግብር መካሄዱን ሲቀጥል 12 ሠዓት ላይ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይጫወታሉ፡፡

Exit mobile version