Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ካምፓላ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በአፍሪካ ህብረት ልዩ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ በዛሬው ዕለት ዩጋንዳ ካምፓላ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ  ኢንተቤ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሀገሪቱ መከላከያና የአርበኞች ጉዳይ ሚኒስትር ጃኮብ ማርክሰንስ ኦቦት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ታዬ በቆይታቸው በአፍሪካ አስተማማኝ የግብርናና የምግብ ሥርዓት መገንባት በሚል መሪ ሃሳብ በሚካሄደው የድህረ ማላቦ አጠቃላይ የአፍሪካ ግብርና ልማት ፕሮግራም አፈጻጸም መድረክ ላይ ይሳተፋሉ፡፡

Exit mobile version