የሀገር ውስጥ ዜና

የፌዴራልና የክልሎች የፋይናንስ፣ የገቢዎች፣ የፕላንና ልማት የምክክር መድረክ ተጀመረ

By Feven Bishaw

January 10, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራልና የክልሎች የፋይናንስ፣ የገቢዎች፣ የፕላንና ልማት 29ኛው የምክክር መድረክ በጅማ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ውይይቱ ተግባራዊ እየተደገ ባለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም፣ በመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት፣ በሀገራዊ የልማት እቅድ እና በገቢ ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የሀገር ውስጥ ገቢን ማሳደግ፣ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ላይ በመመስረት ዘላቂና አስተማማኝ በሆነ መልኩ ሀገሪቱ ቅድሚያ የሰጠቻቸውን የልማት ፕሮግራሞች ፋይናንስ ለማድረግ ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የተሟላ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ውጤታማነት በማረጋገጥ ረገድ ከፌዴራል እስከ ታችኛው የመንግስት መዋቅር ድርስ ርብርብ ማድረግ ይጠበቃል ማለታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ማሻሻያ ስራዎች ያመጡት ለውጦች ተገምግመው የተገኙት ውጤቶች አበረታች መሆናቸውም በመድረኩ ተገልጿል፡፡