Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሐረሪ ለኮሪደር ልማት ሥራ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረሪ ክልል መሥተዳድር ምክር ቤት ለኮሪደር ልማት ሥራ 213 ሚሊየን ብር ተጨማሪ በጀት ማጽደቁ ተገለጸ፡፡

ምክር ቤቱ የ2017 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ዕቅድ አፈጻጸምን መነሻ በማድረግ የቀረበለትን የበጀት ክለሳ ማጽደቁ ተገልጿል፡፡

የበጀት ክለሳው በካፒታል አፈፃፀማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ፕሮጀክቶችን በመለየት የላቀ ማህበራዊ ፋይዳ ላለው ተግባር በዋናነት ለኮሪደር የሚውል መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version