ሩሲያ ለኢትዮጵያ የስንዴ ድጋፍ አደረገች የሚለዉ መረጃ የተሳሳተ ነዉ።
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያ ከተለያዩ ሀገራት ተሰባስበው ኢትዮጵያ ውስጥ በጋምቤላ ክልል ተጠልለው ለሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች እንዲውል ዓለም ምግብ ፕሮግራም (ደብሊውኤፍፒ) ያደረገችውን ድጋፍ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ተደረገ በሚል የተዛባ መረጃ በመሰራጨት ላይ ይገኛል።
የሩሲያ መንግስት እንዳስታወቀው ለዓለም ምግብ ፕሮግራም ያደረገው 1 ሺህ 632 ቶን የስንዴ ድጋፍ ኢትዮጵያ ደርሷል የሚል ነዉ።
እዉነታዉ ይሄ ሆኖ ሳለ በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን እና የማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለዉ መረጃ ሀሰት መሆኑ ተረጋግጧል።
የሩሲያ ድጋፍ አዳማ ሲደርስ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር የቭጌኒ ተረክሂን ተገኝተው ለዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አስረክበዋል።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በጋምቤላ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በገንዘብ እጥረት ምክንያት 60 በመቶ የሰብዓዊ ድጋፍ ያገኙ እንደነበር ገልፆ፣፤ ሩሲያ ያደረገችው የስንዴ ድጋፍ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አስታውቋል፡፡