የሀገር ውስጥ ዜና

በርዕደ መሬቱ 37 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት ደረሰ

By yeshambel Mihert

January 09, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል ጋቢ ዞን እየተከሰተ ባለው ተከታታይ ርዕደ መሬት በሶስት ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ 37 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሃላፊ አቶ አብዱ ሀሰን ያዮ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለፁት÷ በጉዳቱ ሙሉ በሙሉ የወደሙ እና በከፊል ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡

16 ትምህርተ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ጉዳት ሲደርስባቸው 21 ትምህርት ቤቶች ደግም ከፊል ጉዳት እንደረሰባቸው ነው ሃላፊው የገለፁት፡፡

የክልሉ መንግስት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዳይርቁ በክልል ደረጃ ኮሚቴ በማቋቋም ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

ጉዳቱ የደረሰው በአዋሽ-ፋንታሌ፣ ዱላሳ እና ሓንሩካ ወረዳዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በአፋር ክልል አዋሽና አካባቢው 5.3 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የርዕደ መሬት አደጋ መከሰቱ ይታወቃል፡፡

በአሊ ሹምባህሪ