Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለማኅበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የነበሩ ሴቶች የክኅሎት ስልጠና ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የተገነባው የነገዋ ሴቶች ተሃድሶና ክኅሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ለማኅበራዊ ችግሮች ተጋልጠው የነበሩ 400 የሁለተኛ ዙር ሴት ሰልጣኞችን መቀበሉ ተገለጸ፡፡

ለሴተኛ አዳሪነት እና ለተለያዩ ማኅበራዊ ችግሮች ተጋልጠው የነበሩ 400 ሴቶች ስልጠና መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ከ300 በላይ ሴቶች በ17 ዓይነት ዘርፎች ሰልጥነው የሙያ ባለቤት መሆናቸውን አውስተዋል፡፡

Exit mobile version