የሀገር ውስጥ ዜና

ኢግልድ 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ለገበያ አቀረበ

By Melaku Gedif

January 09, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ባለፉት አምስት ወራት 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ለገበያ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ፥የኢግልድ ዋና አላማ በገበያ ላይ ጠንካራ የአቅርቦትና ግብይት ሰንሰለት መፍጠር ነው፡፡

በዚህ መሰረትም መንግስት ቅድሚያ በሰጣቸው ዘርፎች ለተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ጥሬ እቃና የተለያዩ ግብዓቶችን እያቀረበ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የዋጋ ንረትን በማረጋጋት አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ባለፉት አምስት ወራትም 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸው የተለያዩ ምርቶችን ለገበያ ማቅርቡን ነው ያስረዱት፡፡

በዚህም ጥራት ያለው ምርትን ለገበያ ከማቅረብ ባለፈ የዋጋ ንረትን ከማረጋጋት አንጻር ጉልህ ሚና መጫወቱን አስገንዝበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ