Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ አረጋ ከበደ በቃሉ ወረዳ የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶችን እየመረቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ከ143 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በተገኙበት እየተመረቁ ነው።

ከፕሮጀክቶች መካከልም የመስኖ አውታር፣ የድልድይና የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

የመስኖ ፕሮጀክቱ ከ250 ሄክታር መሬት በላይ በማልማት 370 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተጠቁሟል።

ለፕሮጀክቶቹ ግንባታ ከ143 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን÷ የአካባቢው ነዋሪዎችን የልማት ፍላጎት መሰረት ተደርጎ የተገነቡ እንደሆኑ ተመልክቷል።

Exit mobile version