አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ኢ) በአየር ሀይል አካዳሚ ወታደር ማሰልጠኛ ት/ቤት የሰለጠኑ የ8ኛ ዙር የአየር መንገድ ሰልጣኞች ተመረቁ።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢፌዲሪ አየር ኃይል ም/አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ነገራ ለሊሳ÷ ሀገር ታላቅ ህዝብን በሚመጥን መልኩ እየተገነባች ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኩራት የሆነው አየር መንገድን ለሚቀላቀሉ ሰልጣኞች ሀገርን ማወቅ እንደሚገባቸው አስገንዝበው፤ ሀገርን ማወቅ ለራስም ለሀገርም አኩሪ ታሪክ ለመፃፍ ያግዛል ብለዋል፡፡
ታላቅ ህዝብ በሚል የተሰየመው የሰልጣኞቹ ምርቃት ሀገርን ማወቅ ማስተዋወቅ በፈተና ውስጥ መሻገር በፅናት ማለፍ እንደሚገባ ትምህርት የተወሰደበት መሆኑን ተነግሯል፡፡
ሰልጣኞቹ ከ200 በላይ ሲሆኑ በአንድ ወር የስልጠና ቆይታቸው የአካል ብቃት፣ የስነልቦና ግንባታ እና የሀገር ፍቅር ስልጠና መውሰዳቸው ተጠቁሟል፡፡
በአካዳሚው በስምንት ዙር ከ1 ሺህ 400 በላይ ሰልጣኞች ስልጠናውን መውሰዳቸው ተመላክቷል፡፡
በፈትያ አብደላ