Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ የሚገነባው ጋምቤላ ቤተ-መጻሕፍት ….

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ በሚገኝ ገቢ በጋምቤላ የሕዝብ ቤተ-መጻሕፍት ሊገነባ ነው፡፡

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ልዩ አማካሪ ብርሃኑ ደጀኔ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ከመጽሐፉ ሽያጭ በሚገኝ ገቢ ከመሬት በላይ ባለሁለት ወለል ቤተ-መጻሕፍት ለመገንባት የዲዛይን ሥራ ተጠናቅቆ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

እስከ አሁንም ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ቃል መገባቱን እና ከዚህ ውስጥ ከ9 ነጥብ 7 ሚሊየን የሚልቀው ወደ ተዘጋጀው ዝግ አካውንት ገቢ መደረጉን አረጋግጠዋል፡፡

በቅርቡ ደግሞ ከሴክተር ተቋማት፣ ዞን እና ወረዳዎች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚሰበሰብ ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይ ጨረታ በማውጣት የግንባታ ሥራው እንደሚጀመርም ነው አቶ ብርሃኑ ያስታወቁት፡፡

ቤተ-መጻሕፍቱ ለትውልድ ያለውን ጥቅም በመገንዘብ ሕብረተሰቡ፣ ባለሃብቶች፣ ተቋማት እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በመጻሕፍቱ ግዥ ላይ በንቃት እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

Exit mobile version