Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

መሠረተ-ልማቶችን የማዛወር ሥራ በዚህ ወር መጨረሻ ይጠናቀቃል- አገልግሎቱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ኢ) በኮሪደር ልማቱ የሚዛወሩ መሠረተ-ልማቶችን እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ለማጠናቀቅ እየሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት በ14 ከተሞች የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማት የማዛወር እና መልሶ ግንባታ ሥራ እያከናወነ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል፡፡

እስከ ሕዳር 30 ድረስ 3 ሺህ 275 የምሰሶ እና 96 የማሰራጫ ትራንስፎርመሮች ማዛወር ሥራ ማከናወኑንም በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በአዲስ አበባ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ እና ድሬዳዋ 13 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የመሬት ውስጥ ተቀባሪ መስመር እና አምስት ስዊቺንግ ስቴሽኖችን የማዛወር ሥራ ማከናወኑን ነው የገለጸው፡፡

የኮሪደር ልማቱ በአዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ ባሕርዳር፣ ደሴ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረሪ፣ ሠመራ፣ ሻሸመኔ፣ ቢሾፍቱ፣ ጅማ፣ አምቦ፣ ሐዋሳ፣ አርባምንጭ እና ሸገር ከተሞች እየተከናወነ እንደሚገኝም አብራርቷል፡፡

Exit mobile version