አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅማ ዞን ኦሞ ናዳ ወረዳ አንዲት እናት 6 ነጥብ 2 ኪሎ ግራም የሚመዝን ልጅ ተገላግላለች፡፡
ህጻኑ በናዳ ሆስፒታል በቀዶ ጥገና መወለዱን በሆስፒታሉ የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ዶክተር ደሳለኝ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ህጻኑ እና ወላጅ እናት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ኦቢኤን ዘግቧል፡፡
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1879 በአሜሪካ ኦሃዮ ግዛት 9 ነጥብ 98 ኪሎግራም የሚመዝን ህጻን ልጅ የተወለደ ሲሆን ÷ይህም የዓለም ክብረ ወሰን በመሆን ቀጥሏል፡፡
ህጻኑ ከተወለደ ከ11 ሰዓት በኋላ ሕይወቱ ማለፉም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ጤናማ አዲስ የሚወለድ የህጻን ልጅ አማካኝ ክብደት 3 ነጥብ 4 ኪሎ ግራም መሆኑን የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡