Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባህርዳር ከተማ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህርዳር ከተማ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ባህርዳር ከተማ በጄሮም ፍሊፕ ብቸኛ ጎል ሀዋሳ ከተማን 1 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም የጣና ሞገዶቹ ነጥባቸውን ወደ 22 ከፍ በማድረግ ሀድያ ሆሳዕናን በግብ ክፍያ በልጠው ሊጉን በጊዜያዊነት መምራት ጀምረዋል፡፡

በተመሳሳይ 12 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡

Exit mobile version