አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የባህልና ኪነ-ጥበብ ፌስቲቫልን ለማዘጋጀት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ገለጹ።
ሚኒስትሯ እንደገለጹት ፥ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሉ ባህላዊና ኪነ-ጥበባዊ እሴቶች ገዢ ትርክትንና ብሔራዊነትን ይበልጥ ማስረጽ እንዲችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው።
ለአብነትም ለሦስት ወር ሲካሔድ የቆየው ሀገር አቀፍ የኪነጥበብ ንቅናቄ አንዱ መሆኑን ገልፀው ንቅናቄው የዜጎችን አብሮነት የሚሰብኩ፣ የሀገር ገጽታን የሚገነቡና የሚያስተዋውቁ የኪነ-ጥበብ ስራዎችን ማጉላቱን ጠቁመዋል፡፡
በቀጣይም የምስራቅ አፍሪካ የባህልና ኪነ-ጥበብ ፌስቲቫልን ለማዘጋጀት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይህ ስራ የኢትዮጵያን ገጽታ ለመገንባት ብሎም ለትውልዱ ከጥላቻ የጸዳች ሀገር የማስረከብ ስራ መሆኑን መረዳትና ለስኬታማነቱ መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
በተለይም ከኪነ-ጥበብ ባለሙያው ጋር በቅርበት መስራትና በሚያግባቡ ጉዳዮች ላይ የሚከናወኑ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር ወሳኝ ነው ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።