Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአማራ ክልል እስካሁን 83 ሚሊየን ኩንታል ምርት ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ታህሣሥ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ከልል በ2016/17 የምርት ዘመን ከመኸር እርሻ እስካሁን ከ83 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የሰብል ልማት ባለሞያ እንዬ አሰፋ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክልሉ በመኸር እርሻ ሥራ ከ5 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በሰብል ተሸፍኗል፡፡

እስካሁን ድረስም 4 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ የለማ ሰብል በኮምባይነር፣ በመውቂያ መሳሪያና በባህላዊ መንገድ መሰብሰቡን ጠቁመዋል፡፡

ከመኸር እርሻ እስካሁን ባለው ሒደት 83 ሚሊየን ኩንታል ምርት የተሰበሰበ ሲሆን÷ 4 ሚሊየኑ በኮምባይነርና በመውቂያ መሳሪያ መሰብሱን አንስተዋል፡፡

የምርት ብክነትን ለመቀነስም ለአርሶ አደሩ አስፈላጊውን እገዛ ከማድረግ ባለፈ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መከናወኑን ነው ያስረዱት፡፡

በመላኩ ገድፍ

Exit mobile version