Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በትግራይ ክልል 13 ሚሊየን ኩንታል ምርት ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል በ2016/17 የምርት ዘመን 13 ሚሊየን ኩንታል ምርት ተመሰብሰቡን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ኢያሱ አብረሃ (ዶ/ር) እንደገለፁት÷በምርት ዘመኑ የማስፈፀም አቅምን በማሳደግ የክልሉን ምርታማነት በመጠንና በጥራት ለማሳደግ ሰፊ ስራ ተሰርቷል።

በ2016/17 የምርት ዘመን 20 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዶ 13 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን ነው የተናገሩት፡፡

ክልሉ ለግብርና ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱና የፌደራል መንግስት ግብዓቶችን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉ ለተገኘው ምርት አስተዋጽኦ ነበረው ብለዋል።

በቀጣይ የምርት ዘመን የሚታረስ መሬትን በማስፋትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የተሻለ ምርት ለመሰብሰብ ዝግጅት እንደሚደረግ ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version