የሀገር ውስጥ ዜና

የአእላፋት ዝማሬ የምስጋና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

By Mikias Ayele

January 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁለተኛው የአእላፋት ዝማሬ የምስጋና መርሐ ግብር በቦሌ ደብረ ሳሌም መድሃኒዓለም ካቴድራል እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ እና ሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል፡፡

የጃንደረባው ትውልድ ማኅበር ባዘጋጀው የአእላፋት ዝማሬ የምስጋና መርሐ ግብር ላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናንና ምዕመናት ተሳትፈዋል፡፡