የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አደም ፋራህ ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Feven Bishaw

January 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የገና በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አቶ አደም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ” ብለዋል።

በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡