Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ማንቼስተር ሲቲ በሰፊ የግብ ልዩነት ሲያሸንፍ ቼልሲ ነጥብ ጥሏል

አዲስ አበባ፣ ታህሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር ማንቼስተር ሲቲ ዌስትሃም ዩናይትድን 4 ለ 1 ሲያሸንፍ ቼልሲ ከክሪስታል ፓላስ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡

ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ለማንቼስተር ሲቲ የማሸነፊያ ግቦቹን ኩፋል በራሱ ግብ ላይ እንዲሁም ኧርሊንግ ሃላንድ (2) እና ፊል ፎደን ሲያስቆጥሩ÷ ለዌስትሃም ብቸኛዋን ግብ ኖኮላስ ፉልክሩግ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ወደ ሴልሁሩስት ፓርክ ያቀናው ቼልሲ ከክሪስታል ፓላስ ጋር 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታውን አጠናቅቋል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ብሬንትፎርድ ሳውዝሃምፕተንን 5 ለ 0፣ አስቶንቪላ ሌስተር ሲቲን 2 ለ 1 እንዲሁም ቦርንማውዝ ኤቨርተንን 1 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡

ምሽት 2 ከ30 ላይ በሊጉ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አርሴናል ከብራይተን የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

 

Exit mobile version