Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች ተገደሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡

የጋዛ ንጹሃን መከላከል ኤጀንሲ በጥቃቱ በከተማዋ የሚገኙ የመኖሪያ ህንጻዎች መውደማቸውን ጠቁሟል፡፡

በጥቃቱ ዙሪያ ከእስራኤል ወገን እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡

በጋዛ የጤና ተቋም እንዳስታወቀው ባለፉት 24 ሰዓታት እስራኤል በወሰደችው የአየር ጥቃት 59 ሰዎች ሲገደሉ 270 ሰዎች ደግሞ የተለያየ መጠን የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

እስራኤል እና ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ በአሜሪካ፣ ግብጽ እና ኳታር አደራዳሪነት በዶሃ እየተካሄደ መሆኑን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።

 

Exit mobile version