አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለተከታታይ አምስት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ክለቦች የአጭር፣ መካከለኛ፣ የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ርምጃ እና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቋል፡፡
ሻምፒዮናውን በሴትም በወንደም ድምር ውጤት የኢትዮጵያ ንግድ 319 ዋንጨዋችን በመሰብሰብ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ፣ መቻል 315 ዋንጫዎችን በመሰብሰብ ሁለተኛ እንዲሁም ሸገርሲቲ 162 ዋንጫዎችን በመሰብሰብ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡
በሻምፒዮናው ፍፃሜ ላይ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ጌቱ ገረመውን ጨምሮ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።