አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በጅማ ዞን የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ የመንግስት ኮሙኒኬሸን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፣ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) እና በብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ፍቃዱ ተሰማን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።
ሃላፊዎቹ በጅማ ዞን መና ወረዳ የልማት ሥራዎችን እንዲሁም የገጠር ኮሪደር ልማት እና በኬላ ጉዳ እየለማ የሚገኘውን የሻይ ልማት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡