አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል ዓመታዊ የእንቁላል የምርት ግምት 56 ሚሊየን መድረሱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
በጅግጅጋ ከተማ ብሔራዊውን የሌማት ትሩፋት ሥራ በትጋት እየተገበረ ያለው የሆርን አፍሪክ የዶሮ ርባታ ማዕከል 52 ሺህ ዶሮዎች በማርባት 35 ሺህ እንቁላሎችን በቀን እያመረተ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
ሀገር አቀፉ ንቅናቄ ከመጀመሩ አስቀድሞ አጠቃላይ የክልሉ ዓመታዊ የእንቁላል ምርት 3 ነጥብ 5 ሚሊየን እንደነበር ተመላክቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት ያለው የክልሉ ዓመታዊ የእንቁላል የምርት ግምት 56 ሚሊየን መድረሱንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡