አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጅግጅጋ በነበራቸው ቆይታ በከተማዋ በመካሄድ ላይ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ጎብኝተዋል፡፡
በማደግ ላይ ያለችውና ዐቢይ ማዕከል ለመሆን ከፍተኛ አቅም ያላት ጅግጅጋ 30 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ እያካሄደች እንደምትገኝ ተገልጿል፡፡
ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በጅግጅጋ የኮሪደር ልማቱን የመጀመሪያ ምዕራፍ የ10 ኪሎ ሜትር ሥራ ተዘዋውረው እንደተመለከቱም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡