አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተለይም በበዓል ሰሞን በዲጂታል ከፍተኛ የግብይት እንቅስቃሴ እንደሚኖር ይታወቃል፡፡
በዓሉን በማስታከክም ከሕጋዊ ተቋማት የተላኩ የሚመስሉ “በዓሉን በማስመልከት ስጦታ አሸንፈዋል”፣ “ለሽልማት ተመርጠዋል” እና ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ሐሰተኛ መልዕክቶች ለግለሰቦች ሲላኩ ይተስተዋላል፡፡
ይህን ተከትሎ ከሚመጣ የሳይበር ጥቃት ስጋት ራስን ለመጠበቅም የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች መተግበር እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ይመክራል፡፡
1. ሞባይልዎን (የመገልገያ መሣሪያዎችዎን)/ መቆለፍ
2. ሐሰተኛ የክፍያ ማረጋገጫ የጽሑፍ መልዕክቶችን መጠንቀቅ
3. የባንክ ሒሳብ ሁኔታን (ታሪክ) በየጊዜው መፈተሽ (መመልከት)
4. ደንበኞች ግብይት (ክፍያዎች) በሚፈጽሙበት ጊዜ ወዲያውኑ ክፍያ እንደፈፀሙ የሚያሳውቁ መልዕክቶች ወደ ስልካቸው እንደደረሳቸው ማረጋገጥ
5. የሕዝብ ዋይፋይ አለመጠቀም
6. የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያን ማዘመን
7. ሞባይል ላለመጠቀም ወይም ለሌላ ሰው መስጠት ሲያስፈልግ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያውንና ታሪኩን ማስወገድ እንዲሁም ምስጢራዊ መረጃዎችን ማጥፋት ይገባል፡፡