የሀገር ውስጥ ዜና

አስተዳደሩ ከጂያንግሱ ግዛት ጋር በተለያዩ ዘርፎች በትብብር ለመስራት መግባባት ላይ ደረሰ

By yeshambel Mihert

January 03, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጂያንግሱ ግዛት ጋር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፎችን ጨምሮ በትብብር ለመስራት መግባባት ላይ ደረሰ።

ከንቲባዋ ከቻይና ጂያንግሱ ግዛት አስተዳዳሪ ሹ ኩንሊን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን በማህበራ ትስስር ገጻቸው አመልክተዋል።

ሹ ኩንሊን በህዳር ወር በአዲስ አበባ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የጂያንግሱ ግዛትን እንድንጎበኝ ባቀረቡልን ግብዣ መሰረት በግዛቱ ተገኝተን እየጎበኘን ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በጉብኝታችን ወቅት ከጂያንግሱ ግዛት አስተዳዳሪ እና አመራሮች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በመወያየት በቀጣይ በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በቱሪዝም፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፎች ላይ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እና በቀጣይም በትብብር ለመስራት ተግባብተናል ብለዋል።

ሹ ኩንሊን በጂያንግሱ ግዛት በነበራቸው ጉብኝት ላደረጉት መስተንግዶም አመስግነዋል፡፡