Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡

ይህን ተከትሎም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ለፋና ዲጂታል አረጋግጠዋል፡፡

በዚሁ መሠረት በተቀናጀ ሁኔታ ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የማጓጓዝ ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ አሁንም በተደጋጋሚ መቀጠሉን ጠቅሰው÷ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ዛሬ ተከስቷል፤ ንዝረቱም ከሰሞኑ ከፍያለ እና ጠንካራ ነበር ብለዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

Exit mobile version