የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ሙስጠፌ መሀመድ የጎዴ -ቀላፎ የአስፓልት መንገድ ግንባታ ሂደትን ጎበኙ

By Feven Bishaw

January 02, 2025

 

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ከተለያዩ የክልሉ አመራሮች ጋር በመሆን የጎዴ -ቀላፎ የአስፓልት መንገድ የግንባታ ሂደትን ጎብኝተዋል።

የጎዴ -ቀላፎ የአስፓልት መንገድ ግንባታ 95 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ÷ የመንገዱ ግንባታ አፈፃፀም ከ65 ከመቶ በላይ መድረሱ ተገልጿል።

የርዕሰ መስተዳድሩ ጉብኝት የመንገዱ ግንባታ የስራ ሂደትን እና የመንገዱ ግንባታ ጥራት ለመመልከት ያለመ መሆኑን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል።