Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ብሪክስ 9 ሀገራትን በአጋርነት ተቀበለ

BRICS summit flags with all new members BRICS. 3D rendering isolated on white background

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፈረንጆቹ አዲሱ ዓመት መጀመሪያ ብሪክስ ዘጠኝ አዳዲስ አገሮችን በአጋርነት ተቀብሏል።

እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2024 በካዛን ሩሲያ በተካሄደው 16ኛው የብሪክስ ጉባኤ 13 ሀገራት የብሪክስ አጋር እንዲሆኑ ግብዣ ቀርቦላቸው ነበር፡፡

ከነዚህም መካከል ዘጠኝ ማለትም ቤላሩስ፣ ቦሊቪያ፣ ኩባ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ካዛኪስታን፣ ማሌዥያ፣ ታይላንድ፣ ኡጋንዳ እና ኡዝቤኪስታን በሪክስን በአጋርነት የተቀላቀሉት ሀገራት መሆናቸው ታውቋል።

የአዳዲሶቹን አጋር ሀገራት አባልነት ይፋ ለማድረግ ከነባር አጋር ሀገራት ጋር ምክክር እንደሚደረግ ዘ ሳውዝ አፍሪካን ዘግቧል።

Exit mobile version