አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ 39ኛው የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ካርተር ታላቅ የሀገር መሪና ለብዙዎች አርዓያ እንደነበሩ ገልፀዋል፡፡
ካርተር ስለዓለም ሰላም በነበራቸው ግንዛቤና እዝነት ሲታወሱ እንደሚኖሩም አንስተዋል፡፡