Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አርሰናል ብሬንትፎርድን በሜዳው አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ19ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወደ ጌቴክ ኮሚኒቲ ስታዲየም ያቀኑት መድፈኞቹ ብሬንትፎርድን 3 ለ 1 አሸንፈዋል፡፡

ምንም እንኳን ንቦቹ በብሪያን ሙቤሞ ግብ ሲመሩ ቢቆዩም÷ ጋብሬል ጀሱስ፣ ሚኬል ሜሪኖ እና ጋብሬል ማርቲኔሊ ለመድፈኞቹ ባስቆጠሯቸው ጎሎች 3 ለ 1 ተረትተዋል፡፡

39 ነጥቦችን የሰበሰበው አርሰናል ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ፕሪሚየር ሊጉን ከሚመራው ሊቨርፑል ያለውን ልዩነት ወደ ሥድስት ዝቅ በማድረግ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

Exit mobile version