ቢዝነስ

ፍትሓዊ የሀብት ክፍፍልን ማስፈንና የዋጋ ግሽበትን በነጠላ አሃዝ ለማቆየት ታቅዷል- አቶ አህመድ ሽዴ

By Tibebu Kebede

July 23, 2020

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያን ማዕከል በማድረግ ፍትሓዊ የሀብት ክፍፍል ማስፈንና የዋጋ ግሽበትን በነጠላ አኅዝ ለማቆየት መታቀዱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ገለጹ።

ዘላቂ የልማት ፋይናንስ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል። ሚኒስትሩ ውጥኑን ባቀረቡበት ወቅት በኢትዮጵያ አሁንም በርካታ ዜጎች ከድህነት ወለል በታች ይኖራሉ ብለዋል።