Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሕገ-ወጥ ነዳጅ ግብይት በተሳተፉ አካላት ላይ ርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በነዳጅ ግብይት ሥርዓት በሚስተዋሉ ሕገ-ወጥ ድርጊቶች ላይ ሕጋዊና አስተዳደራዊ ርምጃ መወሰዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)÷የነዳጅ ግብይትን ሕጋዊነት ለማረጋገጥ በትኩረትና በትብብር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም ባለፉት ጥቂት ወራት በተካሄደ የቁጥጥር ስራ 34 የሚሆኑ የነዳጅ ማደያዎች ርምጃ እንደተወሰደባቸው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

በሕገ-ወጥነት ሲዘዋወር የነበረ 385 ሺህ 947 ሊትር ነዳጅ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ጠቁመው÷ከዚህም 27 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ መደረጉን ጠቅሰዋል።

ከዲጂታል ግብይት ውጭ በእጅ የእጅ ክፍያ መሸጥ፣ አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ነዳጅ በየማደያው እያለ አገልግሎት አለመስጠትና በክምችት ካላቸው ነዳጅ ቀንሰው ለተቆጣጣሪ አካል ሪፖርት ማድረግ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥ ተግባራት ናቸው ብለዋል፡፡

ረጃጅም ሰልፎች በየከተሞች የሚታይበት ሁኔታ ቢስተዋልም በተጨባጭ ግን የቤንዚን አቅርቦት ችግር አለመኖሩን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

Exit mobile version