Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሜሪካ ለዩክሬን 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ለመደገፍ ቃል ገባች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ ለዩክሬን 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ልታደርግ ነው፡፡

ድጋፉዩክሬን ከሩሲያ ከሚሰነዘርባት ጥቃት ራሷን እንድትከላከል ያግዛታል ተብሏል፡፡

በፈረንጆቹ ጥር 20 ቀን 2025 ከነጩ ቤተመንግስት የሚወጡት ጆ ባይደን “በቀሪው የስልጣን ቆይታዬ በጦርነቱ አሜሪካ የዩክሬንን አቋም ለማጠናከር ያላሰለሰ ጥረት ማድረጓን ትቀጥላለች” ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ቀደም ብለው ከአሜሪካ የሚገኘው ድጋፍ የሩሲያን ጥቃት ለመቋቋም ጥረት ለሚያደርገው የዩክሬን ሃይል ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል ማለታቸው ይታወሳል።

ሌሎች አጋሮች ድጋፋቸውን በሚፈለገው ደረጃ እንዲቀጥሉ ለማድረግ እየሰራን ነውም ሲሉም ዘለንስኪ በትናትናው ዕለት ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version