Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከጅቡቲው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዎስ (ዶ/ር) ከጅቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦመር ጊሌ ጋር ውይይት አድርገዋል።

የውይይቱ ዓላማ የትውውቅ እና በሁለቱ ወንድማማች ሀገሮች መካከል ያለውን የቆየ ወዳጅነት ለማጠናከር መሆኑን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ አመላክቷል።

በውይይታቸውም የሁለትዮሽና አህጉራዊ ጉዳዮችን በማንሳት የመከሩ ሲሆን፤ በቅርቡ በተካሄደው 17ኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ላይ በተነሱት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በጋራ ለመስራትም መክረዋል።

ሁለቱ ሀገራት በቀጠናው ያለውን መረጋጋት እና ትብብር ለመደገፍ ተስማምተዋል።

Exit mobile version