Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የማህበርሩ 3ኛ ዓመት የምስረታ ጉባኤ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞው የኢትዮጵያ ፖሊስ ሠራዊት የድጋፍና ልማት ማህበር 3ኛ ዓመት የምስረታ ጉባኤ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እንዳሉት እየተካሄደ ያለው ፖሊሳዊ ሪፎርም ክፍተቶችን እየለዩ በማረም ወደ ሙያዊ የፖሊስ ተቋም በማሳደግ ዘመን ተሻጋሪ ተቋም መፍጠር ነው።

የድጋፍና ልማት ማህበሩ፣ ከፖሊስ ተቋም በዕድሜና በግዳጆች ላይ ጉዳት ደርሶባቸው ጡረታ የሚወጡ የፖሊስ አመራርና አባላት የተሻለ ሥራ አግኝተው ሕይወታቸውን እንዲቀይሩ ያስችላል ማለታቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

Exit mobile version