አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኮሪያ በደረሰ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ቢያንስ የ85 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
175 መንገደኞችንና 6 የበረራ ሰራተኞችን ከታይላንድ ባንኮክ አሳፍሮ ደቡብ ኮሪያ የደረሰው አውሮፕላን ሙአን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ሲሞክር ነው የተከሰከሰው።
በደረሰው አደጋም እስካሁን ቢያንስ የ85 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የሀገሪቱ እሳትና ድንገተኛ አደጋ ኤጀንሲ አስታውቋል።
አደጋው በተከሰተበት ቦታ የሚከናወነው የነፍስ አድን ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል።