አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 40ኛው ዙር የጉሚ በለል መድረክ ከግጭት ወደ ዘላቂ ሰላም በሚል መሪ ሐሳብ ተካሄደ፡፡
የክልሉ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ በመድረኩ ላይ እንዳሉት÷ ከግጭት አዙሪት ለመውጣት በኦሮሚያ ክልል መንግስት በኩል እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተስፋ ሰጪ ናቸው፡፡
የሐሳብ ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እና የመሳሪያ ድምጽ እንዳይሰማ ለማድረግ መንግስት በወሰደው ቁርጠኝነት ውጤት ተገኝቷል ብለዋል፡፡
ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ስትራቴጂ በመንደፍ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበው÷ የሀገሪቱን እድገት ዘላቂ ለማድረግ በተለያዩ አካባቢዎች አስተማማኝ ሰላም ማስፈን ይገባል ነው ያሉት፡፡
በበኃይሉ ባኔ