የሀገር ውስጥ ዜና

የምክር ቤቱ የተፈጥሮ ሃብት፣ የመስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በህዳሴ ግድብ ጉብኝት እያካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

December 17, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢፈዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት፣ የመስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በህዳሴ ግድብ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት በዛሬው እለት ጉብኝታቸውም የታላቁ የህዳሴ ግድብ አፈጻጸም ሂደት ተዘዋውረው በመጎብኘት ላይ እንደሚገኙ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።